በአሁኑ ጊዜ በኢንተርኔት መገበያየት በኢትዮጵያ እየተለመደ መጥቷል። የቤትና የቢሮ ዕቃዎችም እንደ ሐሮት ፈርኒቸር ያሉ አንጋፋ አምራቾች በኢንተርኔት መሸጥ ብሎም ማድረስ ያሉበት ድረስ ማድረስ ችለዋል። የሚከተሉት ጥቂት ጠቃሚ ማወቅ ያሉብን ነገሮች ናቸው።
1. የሚገዙት ዕቃዎች የት እንደሚመረቱና ጥራታቸውን ይወቁ። የት እንደሚመረቱ ካልታወቀ ውበቱ ብቻ የዕቃው ጥራት መገለጫ ሊሆን አይችልም።
2. ክፍያ ከመክፈልዎ በፊት የመረጡት የትና መቼ እንደሚደርስዎ ያረጋግጡ። አንዳንድ የኢንተርኔት ገበያዎች ዕቃው ሳይኖራቸው ሊሽጡ ስለሚችሉ ከመክፈልዎ በፊት ሙሉ መረጃ ይጠይቁ።
3. ማን ንብረቱን እንደሚያደርስ ይወቁ። ዕቃው የሚገዛበት ከተማና የእርስዎ ቦታ የተራራቀ ከሆነ ማድረስ ቀላል ላይሆን ስለሚችል በመጀመሪያ ያረጋግጡ።
4. የግዢውን ደምብ በሚገባ ያንብቡ። ያልገባዎት ነገር ካለ ጠይቀው ይረዱ። ቀድሞ ማወቅ ችግር ቢያጋጥም ምን ማድረግ እንደሚችሉ እንዲያውቁ ይረዳዎታል።
5. የሚገዙት ዕቃና የእርስዎ ቦታ ስፋት ተመጣጣኝ መሆኑን በቅድሚያ ያረጋግጡ።
ሌሎች ብዙ ያልጠቀስናቸው ጠቃሚ ነገሮችን ኮመንት ላይ ይጻፉ።